Wednesday, November 13, 2013
The Supreme Importance of Churchmanship in an Age of Radical Individualism by Saint John Chrysostom
February 5, 2013 at 2:33pm
The Supreme Importance of
Churchmanship in an Age of Radical Individualism by Saint John Chrysostom from
an article Saint John Chrysostom and 21st Century Christians (I dedicate
this especially for those living in atmosphere of INDIVIDUALISM, please read
through you shall see your self inside)
Saint John taught that the κοινωνοία
(communion by intimate participation) of the Church is a profound miracle. When
is the origin of the Church? From where did our sacred community arise,
brothers and sisters? It has no mere human foundation. The apostles did not
simply gather together and come up with the idea of this organization, with certain
goals, members, and dues. Not at all! The Church is the continuation of the
miracle of the Nativity of Christ. The Son of God was enfleshed in the womb of
the Holy Virgin, and born into the world. The Son of God is progressively
enfleshed in the establishment and propagation of the Church in the world. The
Church is His very Body, the miraculous expansion of His Incarnation in the
world. The supernatural origin of the Church is demonstrated, according to St
John Chrysostom, by the miracle that took place on the Precious and Life-Giving
Cross. When our Savior was hanging upon the Cross He was pierced with a spear,
and suddenly blood and water poured out from His sacred side. This blood and
water is Holy Baptism by which one is incorporated into the Church, and the
Holy Eucharist by which one grows in the Church. These holy mysteries came
forth from the side of our Savior in the same way that Eve was taken from the
side of Adam. The Church is the Bride of Christ, and so was taken from His side
while on the Cross as a fruit of His sacred atonement. She is a miracle of new
creation.
Our unity in the Church, according to Chrysostom, is a supernatural wonder. In
the Church we experience an intimate union with Jesus Christ. This
reality of being “in Christ” is the most used image by the great Apostle Paul
in describing the Christian life. The Christian life is a Church life, for it
is by Holy Baptism that we are incorporated into Christ and His Church. As
Christians we possess a unity far greater than that of earthly organizations. We
share a common womb, a common mother in the Church, a common Father in God, a
common table from which we eat our food of everlasting life, a common language
of doxology, a common quest, a common animating spirit, a common ethic, and a
common destiny. This unity is expressed each Divine Liturgy, according
to Saint John Chrysostom, in our partaking of the Holy Eucharist in which
partaking we are actualized together as the Body of Christ. This is the reason
that we celebrate the Holy Liturgy with one single holy chalice. The singular
sacred cup bears witness to our unity. Even should we distribute Holy Communion
in multiple chalices we do not bless multiple chalices. We consecrate one
alone, and then we bring other empty chalices and fill them from the one sacred
chalice.
Our experience of Church is
transformative. The sacredness of our community is
testified to by what actually happens when we gather together around the holy
altar. Divine services are the single most powerful agent in personal holiness.
“Nothing contributes to a virtuous and moral way of life as does the time
you spend here in church.” There is grace behind every action of the Holy
Liturgy. Chrysostom often waxes eloquent concerning the liturgical movements of
the service. When the deacon exclaims “Stand upright,” he is addressing our
souls primarily, and not just our bodies. The preaching sanctifies. The Holy
Eucharist enlivens and flames leap from our mouths, blood is painted on the
doorposts of our bodies and the angel of death passes over us. Nothing is
more precious, more central, more transformative and miraculous, in our human
existence than life in the Church.
With the gift of this sacred
community come sacred obligations to every Christian. True sacred fellowship is
the power of the Church. Listen to the words of Chrysostom, “Let us prefer the
time we spend here in church to any occupation or concern. Tell me this. What
profit do you gain which can outweigh the loss you bring on yourself and your
whole household when you stay away from the religious services? Suppose you
find a whole treasure house full of gold, and this discovery is your reason for
staying away. You have lost more than you found, and your loss is as much
greater as things of the spirit are better than things we see. Attendance in
the divine services greatly encourages your brothers and sisters in the faith
and spiritual battle ... the Church went from 11 to 120 to three thousand to
five thousand to the whole world and the reason for this growth was that they
never left their gathering. They were constantly with each other, spending the
whole day in the temple, and turning their attention to prayers and sacred
readings. This is why they kindled a great fire. We too must imitate them.”
Chrysostom taught that the communal
responsibilities of Christian people far exceeded their merely needing to be
faithful participants in the divine services. He called upon them to
take responsibility for each other, and to function as an authentic family. If
a faithful Christian is friends with a lazy Christian, the faithful one should
go to the lazy one on Sunday, and literally drag him along to liturgy.
While commenting on Psalm 50 Chrysostom stated that if an immoral Christian was
seen by other congregants getting into the communion line the faithful should
report this immediately to the priest so he can exclude him from communion. If
a faithful Christian hears his brother blaspheme he should strike him in the
mouth, and “sanctify his right hand.” The picture of communal responsibility is
clear, and in our individualistic live-and-let-live context, appears extreme.
But Chrysostom holds membership in the Church very high and assumes that there
are many communal responsibilities associated with it designed by a loving God
to work for the salvation of the entire community. And the responsibilities do
not lie solely with the laity. The clergy must be serious pastors. They must
not leave their sheep diseased or in danger. An example of such serious
pastoring can be found in Chrysostom’s own life as a priest at the time of the
tax riots in Antioch. Saint John preached a series of 21 sermons during the
tense days following the riots. During this series Chrysostom sought to reform
his people from the habit of swearing. No less than 15 times did Saint John
address the subject in a period of just a few weeks, sermon after sermon. He
knew his people were growing very weary of him preaching with the same focus,
yet they had not ceased their bad habit and Chrysostom refused to pretend that
they had and move on. Finally, he acknowledged their grievances and assured
them that he could move on very quickly if they wished. They only needed to
stop swearing and then he would move on. It was completely in their hands. He
was a faithful physician, and not a professional or a show-man. He insisted on
bettering his patients. The result was that swearing decreased and Chrysostom
moved on, but a most important point about life in the Church had been
expressed by the Saint. The life we lead in the Church is a life centered on
personal change.
Brother and sisters, many of our
Orthodox people do not have an authentic experience of what true ecclesial life
is. We do not appreciate the miracle of life in the Church, and we content
ourselves with an empty and alienating individualism. An evil spirit of “it’s
just me and Jesus, baby” has permeated much of American Christianity today to
our nation’s detriment. Our faith teaches us that there is no dichotomy
between Jesus and the Church. Our Savior is not a floating head to be communed
with apart from His sacred Body. Churchmanship is at an astonishing low in
our times. Saint John Chrysostom stands at the throne of God ready to
illumine us and our people about the miracle of sacred community, and to save
us from the death of self-worship. This age of individualism and religious game
playing is a time for serious pastoring, revived churchmanship, and sacred
obedience to the Church. May the God Bless us all!
Monday, October 14, 2013
ጸሎት
በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ
ጸሎት ጸለየ፡- ለመነ፣ ጠየቀ አማለደ፣ ማለደ ካለው የግዕዝ ቃል
የወጣ ቃል ነው፡፡ ጸሎት ማለት ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እግዚአብሔርን ማመስገን
መለመን፣ መጠየቅ፣ መማለድ፣ መማፀን ነው፡፡ “ጸሎት ብሂል ተናግሮ ምስለ እግዚአብሔር፡፡” አባታችን አዳምም
ከመላእክት ተምሮ በየሰዓቱ ይጸልይ ያመሰግን ነበር፡፡ ዲያብሎስ በእባብ አድሮ ወደ አዳም በመጣ ጊዜ ጸሎት እያደረገ
ስለነበር ዲያብሎስን ድል ነሥቶታል ሔዋንን ግን ሥራ ፈትታ እግሯን ዘርግታ ስለአገኛት ድል ነስቷታል፡፡
ጸሎት ሰማእታት ከነደደ እሳት፣ ከተሳለ ስለት፣ ከአላውያን
መኳንንት፣ ከአሕዛብ ነገሥታት ከዲያብሎስ ተንኮል እና ሽንገላ ዲያብሎስ በእነርሱ ላይ ከአጠመደው አሽከላ የዳኑበት
ጋሻ ነው፡፡ ኤፌ.6፥10 21 ጸሎት፣ ሰው አሳቡን ለእግዚአብሔር የሚገልጥበት እግዚአብሔርም የሰውን ልመና ተቀብሎ
ፈቃዱን የሚፈጽምበት ረቂቅ ምስጢር ነው፡፡
የጸሎት መሠረቱ “ዕሹ ታገኛላችሁ ለምኑ ይሰጣችኋል ደጁ ምቱ ይከፈትላችኋል” የሚለው የጌታችን ትምህርት ነው ማቴ.7፥7
ጸሎት፡- በሦስት ክፍል ይከፈላል
-
ጸሎተ አኰቴት
-
ጸሎተ ምህላ
-
ጸሎተ አስተብቊዖት
-
ጸሎተ አኰቴት፡- ማለት እግዚአብሔርን ከሁሉም አስቀድሞ ስለተደረገልን ነገር በማመስገን የሚጀመር ጸሎት ነው ይህም ዓይነት ጸሎት የቅዱስ ባስልዮስን የምስጋና ጸሎት የመሰለ ነው፡፡
“ነአኲቶ ለገባሬ ሠናያት ላዕሌነ እግዚአብሔር መሐሪ”
“ለእኛ በጎ ነገርን ያደረገ ይቅርባይ እግዚአብሔር አምላካችንን እናመሰግነዋለን” ይልና ምክንኀያቱን ሲገልጥ
ጠብቆናልና፥ አቅርቦናልና፥ ወደ እርሱም ተቀብሎናልና፥ እስከዚችም ሰዓት አድርሶናልና” ይላል፡፡ /ሥርዐተ ቅዳሴ/
ይህ ጸሎት የምስጋና ጸሎት /ጸሎተ አኰቴት/ ይባላል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን የምስጋና ጸሎት ለፊልጵስዮስ
ክርስቲያኖች ሲጽፍላቸው “ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማልዱም እያመሰገናችሁም ልመናችሁን ለእግዚአብሔር ግለጡ”
ይላል፡፡ ፊል.4፥6 ዳግመኛም “ስለእናንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ ስለተሰጣችሁ ጸጋ
ዘወትር እግዚአብሔርን አመስግነዋለሁ” 1ቆሮ.1፥4 ብሎ ከመለመን አስቀድሞ እግዚአብሔርን ማመስገን አስፈላጊ መሆኑን
አስተምሯል፡፡ በዚህ መሠረት ሰው የተደረገለትን በጎ ነገር ሁሉ በማሰብ ፈጣሪውን ማመስገን ከማመስገንም ቀጥሎ
የሚያስፈልገውን ከፈጣሪው መለመን አስፈላጊ ነው፡፡
ከቅዱስ ጳውሎስ የምንማረው ለእኛ ስለተደረገልን ብቻ ማመስገንን
አይደለም፤ ሌሎች ስለተደረገላቸውም ማመስገን ተገቢ መሆኑን እንጂ፡፡ “ለእናንተ ስለተሰጣችሁ ጸጋ ዘወትር
እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” ሲል ለወገኖቹ ስለተደረገላቸው በጎ ነገር በደስታ ማመስገኑ ነው፡፡ ክርስትና ማለት
ለእኔ ብቻ ማለት ሳይሆን ለሌሎችም መኖር፣ ለሌሎች በተደረገው የእግዚአብሔር ስጦታም ደስ መሰኘት ነው፡፡ ይህን
የምስጋና ጸሎት /ጸሎተ አኮቴት/ ብዙ አባቶች፣ እናቶች ተጠቅመውበታል፡፡ ለምሳሌም ያህል ዘካርያስንና ኤልሳቤጥን
መመልከት እንችላለን፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥ እግዚአብሔር ያደረገላትን በጎ ነገር ስትመሰክር “እግዚአብሔር በዚህ ወራት
ከሰው ስድቤን ያርቅ ዘንድ በጎበኘን ጊዜ እንዲህ አደረገልኝ” ብላለች፡፡ ሉቃ.1፥25 እግዚአብሔር ጎበኘኝ ብላ
ቸርነቱን አደረገለኝም በማለት የተደረገላትን መልካም ስጦታ ዮሐንስን መጽነሷን ገልጣ አመስግናለች፡፡ ዘካርያስም
እንዲሁ አመስግኗል፡፡ “ያን ጊዜም አፉ ተከፈተ አንደበቱም ተናገረ እግዚአብሔርንም አመሰገነ” ሉቃ.1፥65 “ከዚህ
ጊዜ ያደረስከኝ፥ ከደዌ የፈወስከኝ፥ ዮሐንስን የሰጠኸኝ ብሎ ፈጣሪውን አመስግኗል በመቀጠልም ይቅር ያለን ለወገኖቹም
ድኅነትን ያደረገ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን ከባሪያው ከዳዊት ቤት የምንድንበትን ቀንድ
አስነሣልን፡፡” ሉቃ.1፥68 በዘካርያስ ጸሎት ውስጥ ምስጋናውን አስቀድሞ ትንቢቱን አስከትሎ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ
ምስጋናውና ትንቢቱ አምላክ ለእኛ ያደረገው የቤዛነቱን ሥራ በመግለጥ ሲያመሰግን እንመለከታለን፡፡
2. ጸሎተ ምህላ፡-
ጸሎተ ምህላ ስለፈውሰ ሕሙማን …… ስለ ሀገርና ስለነገሥታት ስለ ጳጳሳት፣ ካህናት ዲያቆናት፣ ምዕመናን ሕይወት
ቸነፈር፣ ጦርነት፣ ረሀብ፣ ድርቅ ወይም ሌላ አስጊ ነገር በሆነ ጊዜ በብዛት፣ በማኅበር የሚጸለይ ጸሎት ነው፡፡
የምህላ ጸሎት ሲጸለይ በእስራኤል ላይ ቸነፈር በተነሣ ጊዜ አሮን በሽተኞን ባንድ ወገን ጤነኞችን ባንድ ወገን
አድርጎ የክህነት ልብሱን ለብሶ ማዕጠንተ ወርቁን ይዞ በራስህ የማልክላቸውን አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን
አስበህ የወገኖችህን ኀጢአት ይቅር በል” እንደጸለየላቸው ነው፡፡ ዘኁ.16፥46-50
ዛሬም ካህናት ከጠቀስናቸው አስጊ ነገሮች ማንኛውም በሀገር ላይ ቢመጣ ወደ ሀገር እንዳይገባ ገብቶ ቢሆን ከፍ ያለ ጉዳት እንዳያመጣ የክህነት ልብስ ለብሰው ማዕጠንቱ ይዘው ሥዕለ ማርያም፣ መስቀል አቅርበው ማኅበረ ክርስቲያንን ሰብስበው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን “ስለእኛ ከድንግል ማርያም መወለድህን ስለእኛ መሠቀል መሞትህን አስበህ የህዝብን ኀጢአት ይቅር በል ከመዓት ወደ ምሕረት ተመለሰ” እያሉ በምህላ ይጸልያሉ፡፡
የምህላ ጸሎት መአትን መቅሰፍትን ይመልሳል ጦርን፣ ቸነፈርን ያስታግሳል መሠረቱም፡፡
“ጾም ለዩ ምህላ ስበኩ” ያለው ቃል ነው፡፡ ይህ ጸሎት በሰላም ጊዜ ሰላሙ ዘላቂ እንዲሆን በጦርነት ጊዜ ለመከላከያነት ዋና መሣሪያ ነው፡፡ ስለዚህ አጥብቀን ልንከተለው ይገባል፡፡
የምህላ ጸሎት ነገሠታት ከዙፋናቸው ወርደው ወንድ ሙሽራ ሴት ሙሽራ ከጫጉላቸው፣ ከመጋረጃቸው ለምግብ የደረሱ ልጆች ከምግብ ለምግብ ያልደረሱ ከጡት ተከልክለው ሕዝብ ሁሉ ምንጣፍ ለብሰው አመድ ነስንሰው የሚጸልዩት ከፍተኛ ጸሎት ነው ኢዩ.2፥12-18፣ ዮና.3፥5
3. ጸሎተ አስብቊዖት
ይህ ጸሎት አንድ ሰው ስለሚፈልገው ነገር ቦታ ለይቶ ሱባኤ ገብቶ
የሚጸልየው ጸሎት ነው፡፡ ይህ ጸሎት በተለይ ጣዕመ ጸጋን በቀመሱ በተባሕትዎ፣ በምናኔ በገዳም በሚኖሩ አበው ዘንድ
የተለመደና የሚደረግ ጸሎት ነው፡፡ ወጣንያን እግዚአብሔርን ጠይቀው አድርግ አታድርግ የሚል መልስን አይጠብቁም፡፡
ፍጹማን አባቶች ግን እግዚአብሔር ጠይቀው አድርግ ወይም አታድርግ የሚል ፈቃደ እግዚአብሔርን ሳይቀበሉ የሚያደርጉት
ነገር የለምና ቦታ፣ ጊዜ ወስነው ፈቃደ እግዚአብሔር ይጠይቃሉ፡፡ ይህ ጸሎተ አስተብቊዖት ይባላል፡፡ ይህም ማለት
መላልሶ ደጋግሞ ያለ ዕረፍት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚደረግ ጸሎት ነው፡፡ ለምሳሌ ትልቁ መቃርስ ዓለምን ዞሮ
ለመጎብኘት ለተከታታይ አምስት ዓመታት እግዚአብሔርን ከለመነ በኋላ እየዞረ መካነ ቅዱሳንን እንዲጎበኝ ከእግዚአብሔር
ፈቃድ አግኝቷል በዚህም ከእርሱ ከገድል በትሩፋት የሚበልጡ መናንያን በማግኘቱ መነኮሳትማ እነርሱ እንጂ እኔ
ምንድን ነኝ? እያለ ራሱን እየወቀሰ እንደተመለሰ በመጽሐፈ መነኮሳት ተጽፎ እናገኛለን፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን
“መስተበቊዕ” የሚባል የጸሎት ክፍል፡፡ አለ ይህ ጸሎት በካህናት አባቶቻችን ስለሙታን፣ ስለሕያዋን፣ ስለነገሠታት፣
ስለ ጳጳሳት ስለ ንዑሰ ክርስቲያን፣ ስለ ምእመናን መባዕ ስለሚያቀርቡ ስለነጋድያን፣ ስለዝናም ስለ ወንዞች የሚጸለይ
ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የጸሎት ክፍል ነው፡፡
ጠቅላላውን በቤተ ክርስቲያን የሚጸልዩ ጸሎታት ጸሎተ ፍትሐት፣ ጸሎተ ተክሊል፣ ጸሎተ ህሙማን፣ ጸሎተ ቅዳሴ፣ ጸሎተ ሰዓታት፣ የግል ጸሎት፣ የማኅበር ጸሎት እነዚህ ሁሉ ከላይ ከዘረዘርዓቸው ሦስቱ የጸሎት ክፍሎች አይወጡም፡፡ ከጸሎተ አኰቴት ከጸሎተ ምህላ፣ ከጸሎተ አስተበቊዖት ይመደባሉ፡፡ እነዚህን ጸሎታት በሰቂለ ኅሊና በአንቃዕድዎ /ዐይንን ወደ እግዚአብሔር በማንሳት/ መጸለይ ታላቅ ዋጋ የሚያሰጥ ከሰይጣን ወጥመድ የሚታደግ ሕይወትን የሚስተካከል ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቅ አጋንንትን የሚያርቅ ኀይለ እግዚአብሔርን ለሚጸልየው የሚያስታጥቅ መላእክትን የሚያስመስል ነው፡፡
እኛም ሰውነታችን ከበደል ልቡናችን ከቂም ከበቀል እንዲሁም ከተንኮል ንጹሕ አድርገን ብንጸልይ እንጠቀማለን ጸሎታችን ተሰሚ ልመናችንና ጩኸታችን ግዳጅ ፈጻሚ ይሆናል፡፡ የአባቶቻችን ጸሎት የተቀበለ እግዚአብሔር አምላካችን ጸሎታችንን ይቀበለናል፡፡
ይቆየን
Wednesday, September 4, 2013
የዘመን አቆጣጠር ባሕረ ሐሳብ
Source: Dn. Melaku Ezezew
1. ባሕረ ሐሳብ ማለት ምን ማለት ነው?
ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽም የሐሳብባሕር ማለት ነው፡፡ በዓላት እና አጽዋማትን ለማውጣት የመደመር፣ የመቀነስ፣የማባዛት ስሌትን ብቻ ሳይሆን ሐሳበ ፀሐይን፣ ሐሳበ ወርኅን፣ ሐሳበ ከዋክብትን ሐሳበዐበቅቴን ወዘተ አጠቃሎ የያዘ እንደ ባሕር የሰፋ በመሆኑ የሐሳብ ባሕር ተብሏል፡፡የዘመን አቈጣጠር ማለት ስለማሕበራዊ ኑሮ ጠቄሜታና የሃይማኖት ተግባሮችለማከናወን በሚያገለግል መልኩ ተፈጥሮአዊውን የወቅቶች ክፍፍል እርስ በርሳቸውየማመቻቸት ዘዴ ነው፡፡
![]() |
ማርቆስ ወንጌላዊ
|
ሐሳበ ዘመን የዘመን አቆጣጠርማለት ሲሆን የሐሳበ ዘመን ትምህርትባሕረ ሐሳብ ይባላል፡፡ ባሕረ ሐሳብየሚለው ቃል ሐሰበ ቆጠረ ከሚለው ግስየወጣ ዘመድ ዘር ነው፡፡ ስለዚህ ባሕረሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ወይምዓመተ ዓለም ማለት ነው፡፡ ባሕረሐሳብ መባሉም የባሕር አዝዋሪቱ፣መንገዱን፣ ጥልቀቱና ስፋቱ ረዥምናሰፊ እንደሆነ የባሕረ ሐሳብ ትምህርትምመንገዱን ስፋቱ ልዩ ልዩ በሆነየአጽዋማትና የሱባዔያት ምሥጢርየተሰናዳ ስለሆነ ነው፡፡
Tuesday, August 20, 2013
Wednesday, August 7, 2013
ጾመ ፍልሰታ
IN THE NAME OF
THE FATHER AND THE SON AND THE HOLY SPIRIT, ONE GOD. AMEN.
''Filseta''
is a pre-assumption fast instituted by the apostles. It lasts for
15days and is commonly refferd as ''little lent''. It is a sober and earnest time in which people of all age participate. Even small children
under seven years of age, the sick, and the sojourner, who are normally exempt from the discipline, maintain the fast of the assumption. Apostles continued to be sad and
sorrowful, because of her separation from them, and because they were
left orphans by her; for Our Lord had given them the hope that they
would see her in the flesh. The Ethiopian book of saints-the synaxarium /January 29/ discusses the assumption. Filseta is the time when the faithful examine their lives in light of the purity, holiness, and obedience of the Virgin. In this spirit one fasts,one prays,one dedicates anew his or her life to God.
“ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት” /መዝ.131፥8/
“ተንሥኢ ወንዒ ቅርብትየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ውስተ ጽላሎተ ኰኲሕ ቅሩበ ጥቅም፡፡ አቅራቢያዬ መልካሟ ርግብየ ተነሽ፤ ነዪ፤ በግንቡ አጠገብ ወዳለው ወደ ዋሻው ጥላ፡፡” /መኃ.2፥10-14/
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መቅደሱ፥ ታቦቱ፣ ማደሪያው፣ መንበሩ እናቱ አድርጎ መረጣት፡፡
ስለዚህ ምክንያት አብ ጠበቃት ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን ከርሷ ተዋሐደ መንፈስ ቅዱስ አጸናት፡፡ እመቤታችን በዚህ
ኃላፊ ዓለም ለ64 ዓመት ቆይታለች፡፡ ጥር ሰኞ ይብታል ሰኞ እስከ ሰኞ 8 ሰኞ እስከ ሰኞ 15፣ ሰኞ እስከ ሰኞ
22፣ ሰኞን ትቶ እሑድ ጥር 21 ቀን እመቤታችን አርፋለች፡፡ ሐዋርያት ባጎበር አድርገው ወደ ጌቴ ሴማኒ ይዘዋት
ሲሄዱ አይሁድ “ቀድሞ ልጇን ሰቅለን ብንገድለው ደቀ መዛሙርቱ ተነሣ፣ ዐረገ” እያሉ ሲያውኩን ኖሩ፤ ዛሬ ደግሞ
እርሷን ተነሣች፣ ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን? በእሳት እናቃጥላታለን” ብለው ተነሡ፡፡ ታውፋንያ የሚባል
አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል የታውፋንያን ሁለት እጁን በሰይፍ መትቶ ቀጣው፡፡
በዚህም የታውፋንያ ሁለት እጁ ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ፡፡ ከዚያ በኋላ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌላዊውን
ቅዱስ ዮሐንስ ጨምሮ በደመና ነጥቆ ከገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት፡፡
Tuesday, July 30, 2013
የአብርሃም ዛፍና የአብርሃም ድንኳን
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ለአብርሃም በአንድነት በሦስትነት በተገለጠባት ዛፍና፤ በገባበት ድንኳን ትመሰላለች (ዘፍ ፲፰፥፩-፴፫)፡:
ይኸውም አብርሃም ከደግነቱ ብዛት እንግዳን ከመውደዱ የተነሣ ድንኳኑን በተመሳቀለ ጎዳና ሠርቶ የወጣ የወረደውን ያለፈ ያገደመውን ሲቀበል የሚኖር በሥራው ኹሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ጻድቅ ነበር (ሮሜ ፬፥፩-፫)፡፡ ጽድቁም ሊታወቅ ስድስት ሰዓት ላይ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ፤ በመምሬ ዛፍ ሥር እግዚአብሔር በአንድነት በሦስትነት ተገለጸለት ‹‹ወሶበ አልዐለ አብርሃም አዕይንቲሁ ነጸረ ሠለስተ ዕደወ እለ ይቀውሙ ወርእየ ወሮጸ ለተቀብሎቶሙ እምኆኅተ ኅይመት ወሰገደ ውስተ ምድር›› ይላል ዐይኑን አቅንቶ ሲመለከት፤ ሥላሴ በአምሳለ ዕደው ቆመው አይቶ፤ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤ ከዚኽ በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትኽስ ሞገስ አግኝቼ እንደኾነ ባሪያኽን አትለፈኝ ብዬ እለምናለኍ፤ ጥቂት ውሃ ይምጣላችኍ፤ እግራችኹን ታጠቡ፤ ከዚኽችም ዛፍ በታች ዕረፉ…›› በማለት ተናግሯል፡፡ ‹‹በፊትኽ ሞገስን አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፤ ‹‹ውሃ ይምጣላችኍ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡
ይኽቺ አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፍለው በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን እግዚአብሔር የተገለጠባት ዛፍ፤ አንድነት ሦስትነት በጐላ በተረዳ ነገር የታወቀባት ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድን በድንግልና የወለደች የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ መኾኗን፤ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ እንዚራ ስብሐት መጽሐፉ ላይ
....‹‹አንቲ ውእቱ ዕፀ ድርስ ዘለአብርሃም በርስአኒሁ
....ዘብኪ አጽለለ እግዚአብሔር በሥላሴሁ ››
(ለአብርሃው በእርጅናው ወቅት፤ እግዚአብሔርን በሦስትነት ያስጠለለብሽ የወይራ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት ሲገልጥ፤ ዳግመኛም በዚኹ መጽሐፉ፡-
...‹‹እንቲ ውእቱ ዕፀት ዘነበርኪ ጥቃ ኀይመት፣
...ዘብኪ አጽለሉ ሠለስቱ አጋዕዝት››
(ባንቺ ሦስቱ ጌቶች (ሥላሴ) የተጠለሉብሽ በድንኳን አጠገብ የቆምሽ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት በአንድነቱ ምንታዌ (ኹለትነት)፣ በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) ለሌለበት አምላክ የሦስትነቱ የአንድነቱ ምስጢር መገለጫ የሥላሴ ማደሪያ መኾኗን መስክሯል፡፡
ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ለአብርሃም በአንድነት በሦስትነት በተገለጠባት ዛፍና፤ በገባበት ድንኳን ትመሰላለች (ዘፍ ፲፰፥፩-፴፫)፡:
ይኸውም አብርሃም ከደግነቱ ብዛት እንግዳን ከመውደዱ የተነሣ ድንኳኑን በተመሳቀለ ጎዳና ሠርቶ የወጣ የወረደውን ያለፈ ያገደመውን ሲቀበል የሚኖር በሥራው ኹሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ጻድቅ ነበር (ሮሜ ፬፥፩-፫)፡፡ ጽድቁም ሊታወቅ ስድስት ሰዓት ላይ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ፤ በመምሬ ዛፍ ሥር እግዚአብሔር በአንድነት በሦስትነት ተገለጸለት ‹‹ወሶበ አልዐለ አብርሃም አዕይንቲሁ ነጸረ ሠለስተ ዕደወ እለ ይቀውሙ ወርእየ ወሮጸ ለተቀብሎቶሙ እምኆኅተ ኅይመት ወሰገደ ውስተ ምድር›› ይላል ዐይኑን አቅንቶ ሲመለከት፤ ሥላሴ በአምሳለ ዕደው ቆመው አይቶ፤ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤ ከዚኽ በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትኽስ ሞገስ አግኝቼ እንደኾነ ባሪያኽን አትለፈኝ ብዬ እለምናለኍ፤ ጥቂት ውሃ ይምጣላችኍ፤ እግራችኹን ታጠቡ፤ ከዚኽችም ዛፍ በታች ዕረፉ…›› በማለት ተናግሯል፡፡ ‹‹በፊትኽ ሞገስን አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፤ ‹‹ውሃ ይምጣላችኍ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡
ይኽቺ አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፍለው በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን እግዚአብሔር የተገለጠባት ዛፍ፤ አንድነት ሦስትነት በጐላ በተረዳ ነገር የታወቀባት ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድን በድንግልና የወለደች የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ መኾኗን፤ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ እንዚራ ስብሐት መጽሐፉ ላይ
....‹‹አንቲ ውእቱ ዕፀ ድርስ ዘለአብርሃም በርስአኒሁ
....ዘብኪ አጽለለ እግዚአብሔር በሥላሴሁ ››
(ለአብርሃው በእርጅናው ወቅት፤ እግዚአብሔርን በሦስትነት ያስጠለለብሽ የወይራ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት ሲገልጥ፤ ዳግመኛም በዚኹ መጽሐፉ፡-
...‹‹እንቲ ውእቱ ዕፀት ዘነበርኪ ጥቃ ኀይመት፣
...ዘብኪ አጽለሉ ሠለስቱ አጋዕዝት››
(ባንቺ ሦስቱ ጌቶች (ሥላሴ) የተጠለሉብሽ በድንኳን አጠገብ የቆምሽ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት በአንድነቱ ምንታዌ (ኹለትነት)፣ በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) ለሌለበት አምላክ የሦስትነቱ የአንድነቱ ምስጢር መገለጫ የሥላሴ ማደሪያ መኾኗን መስክሯል፡፡
Sunday, June 23, 2013
ጰራቅሊጦስ
በቤካ ፋንታ
- እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት/ መዝ 118፥24/
ይህች ታላቅ ዕለት ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን አርድእትና ለቅዱሳት ሴቶች የተገለጠባት ዕለት ናት፡፡ እነዚህ ሁሉ በጸሎት ተግተው በሚጸልዩበት ወራት መንፈስ ቅዱስ በተከፋፈሉ የእሳት ልሳን አምሳል የወረደበት ቅዱስ ቀን ነው፡፡
አስቀድሞ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ደብረ ዘይት በተባለ ታላቅ ተራራ ላይ ሳሉ እንዲህ ብሎ አስተምሯቸው ነበር “ኀይልን ከላይ ከአርያም እስክልክላችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም በጸሎት ቆዩ፡፡”/ሉቃ 24፡36/ መቶ ሃያው ቤተሰብም በኢየሩሳሌም ሀገር በምትገኝ በቤተ መቅደስ በአንድነት ሆነው በጸሎት በመትጋት ቆዩ፡፡ ልጆችዬ መቶ ሃያው ቤተሰብ የሚባሉት 12ቱ ሐዋርያት፣ 72ቱ አርድእት/አገልጋዮች/ እና 36ቱ ቅዱሳን አንስት/ሴቶች/ ናቸው፡፡
ከዕርገት በኋላ በአሥረኛው ቀን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ወዳሉበት፣ በጸሎትና በምሥጋና ወደ ሚተጉበት ሥፍራ በእሳት አምሳል /ምሳሌ/ ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጠባቸው፡፡ ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ ምስጢር ተገለጠላቸው፣ ይፈሩ የነበሩት ሐዋርያትም ወንጌልን ለማስተማር ደፋሮች ሆኑ፣ በተለያየ ቋንቋዎች እንዲናገሩ እውቀት ተሰጣቸው፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ተቀበሉ፡፡ ይህንን ታላቅ ኀይል እና ሰማያዊ ስጦታን የሰጣቸውን እግዚአብሔርን በታላቅ ዝማሬና እልልታ አመሰገኑት፡፡
Saturday, June 15, 2013
ዕርገተ ክርስቶስ
በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ
“አልቦ ዘዐርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ ወልደ እጓለመሕያው” ዮሐ.3፥13
ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ ይህ ኃይለ ቃል ክብር ምስጋና ይግባውና ስለጌታችን፣ አምላካችን፣ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት መውረድ ከድንግል ማርያም መወለድ እና የሰውነቱን ሥራ ጨርሶ በክብር ወደ ሰማይ ማረጉን የሚገልጽ ነው፡፡ እንደሚታወቀው አምላካችን ስለሁለት አቢይ ጉዳዮች ሰው ሆኗል፡፡
- ለቤዛነት /ዓለምን ለማዳን/
- ለአርአያነት /ምሳሌነት/
የሰውን ልጅ በመውደዱ ልዑል ባሕርዩን ዝቅ አድርጎ ከሰማይ ወረደ ሥጋ ለበሰ በምድር ላይ ተመላለሰ፤ ምድርን በኪደተ እግሩ ቀደሰ፤ ድውያንን ፈወሰ፤ ፍጹም ሰው እንደ መሆኑ ተራበ ፍጹም አምላክ መሆኑንም ያስረዳ ዘንድ አምስት ገበያ ሕዝብ በአምስት እንጀራ በሁለት ዓሣ አጠገበ ማቴ.14፥19 ለእኛ አርአያና ምሳሌ ለመሆን ዝቅ ብሎ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ ዮሐ.13፥14 እኛም ፍለጋውን እንከተል ዘንድ “አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ለቢፅክሙ” እናንተም ለባልንጀሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉ ብሎ አዘዘ፡፡ መምሕረ ትሕትና ነውና በዚህ ዓይነት መልኩ ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በዚህ ዓለም ኖረ ለሐዋርያት ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ወንጌልን አስተማራቸው ትምህርት በሚገባ ከተረዳለት በኋላ ለድኅነተ ዓለም በማዕከለ ምድር በቀራንዮ ተሰቀለ፡፡
Monday, May 20, 2013
የቅዱስ ያሬድን 1500ኛ የልደት በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ ዐውደ ጥናት ተከፈተ
ዲ/ን መርሻ አለኸኝ(ዶ/ር)
የቅዱስ ያሬድን 1500ኛ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የተዘጋጀ ዐውደ ጥናት በግዮን ሆቴል ሳባ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተከፈተ፡፡ በዐውደ ጥናቱ ላይ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የልዩ ልዩ መምሪያዎች ሓላፊዎች፣ በዋና ዋና አብነት ት/ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንና የመንግሥትና ልዩ ልዩ ተቋማት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው ሊቃውንት ተገኝተዋል፡፡
ቀሲስ ዶክተር ሰሙ ምትኩ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ማኅበሩ ቅዱሳት መካናት ራሳቸውን ችለው የሚተዳደሩባቸውን ዘላቂ የልማት ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በመተግበር ለአብነት መምህራንና ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ ከፍተኛ ሥራ አየሠራ እንደኾነ ከገለጹ በኋላ፤ ሊቁ ለሀገራችን ከሰጠው አበርክቶ አንጻር ማኅበሩ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውን የቅዱስ ያሬድን የ1500ኛ ዓመት የልደት በዓል በሰፊ ዝግጅት ለማክበር እንደወሰነ ገልጸዋል፡፡
Friday, May 10, 2013
የቀኝ ዐይን - ድንግል ማርያም
በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
አፍጣኒተ ረድኤት ማርያም በጊዜ ምንዳቤ ወአጸባ ለዐይን እምቀራንባ፤ አንቲ ውእቱ ረዳኢተ ያዕቆብ በቤተ ላባ፤ በኩሉ ኅሊናሃ ወበኩሉ አልባባ፤ዘኢታፈቅረኪ ነፍስ ትሠሮ እምሕዝባ፡፡
የነገረ ማርያም ሊቅ(Marian Doctor)እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ እመቤታችንን በብዙ ምሳሌ እየመሰለ፣ እየተረጎመና እያመሰጠረ ብዙ ጊዜ አመስግኗታል፡፡ ምንም እንኳን እኛ የምናውቀው የምስጋና ድርሰቱ ለጸሎት የምንጠቀምበት ውዳሴ ማርያም ቢሆንም ከትርጓሜና ከስብከቶቹ ውጪ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ስንኝ ያላቸው የምስጋና ድርሰቶችን(Hymns) መድረሱን ታሪክ ጸሐፊው ሶዝመን መዝግቦልናል፡፡ ከነዚህ የምስጋና ድርሰቶቹ መካከልም ‹‹በእንተ ልደት››(On Nativity) እና ‹‹በእንተ ቤተ ክርስቲያን››(On the Church)በተባሉ ትልልቅ ድርሰቶቹም እመቤታችንን ደጋግሞ ያመሰግናታል፡፡
Sunday, April 28, 2013
ሰሙነ ሕማማት
መምህር ኃይለ ማርያም ላቀው
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት /የሕማማት ሳምንት/ በማለት ትዘክረዋለች፡፡ ሕማማት የሚለው ቃል “ሐመ፤ ታመመ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን የጌታችንና የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማምና ሞቱ የሚዘከርበት ሳምንት ነው፡፡ በሌላም በኩል ይህ ሳምንት ከአዳም እስከ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ የነበሩ ነፍሳት በሲኦል የቆዩበት የአምስት ሺህ አምስት መቶ የመከራ፣ የፍዳና የኩነኔ ዘመን መታሰቢያ ስለሆነ የሕማማት ሳምንት የሚለውን ስያሜ አግኝቷል፡፡ እንደዚሁም ይህ ሳምንት “ቅዱስ ሳምንት” ይባላል” ከሌሎች ሳምንቶች ሁሉ የተለየ የከበረ ነውና፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሳምንት በእያንዳንዱ ዕለት ስለ ፍጹም ፍቅር የተከፈለ የመሥዋዕትነት ሥራ ስለ ተሠራበት፣ የሰው ልጆች ደኅንነት ስለ ተፈጸመበት፣ መድኀኔዓለም ስለ እኛ ቤዛ ሆኖ ለመስቀል ሞት ታዛዥ ሆኖ ነፍሱን ስለ ካሠልን “ቅዱስ ሳምንት” ተብሏል፡፡ በተጨማሪም “የመጨረሻ ሳምንት” ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በሙዓለ ሥጋዌው ለፈጸማቸው የቤዛነትና የአርአያነት ተግባራት ፍጻሜ በመሆኑ ነው፡፡
በዚህ ልዩ በሆነ ሳምንት ካህናትና ምእመናን በነግህ፣ በሠልስት፣ በቀትር፣ በተሰዓትና በሠርክ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመጓዝ ስለ ጌታችን ኢየስስ ክርስቶስ ሕማማተ መስቀል የሚያዘክረውን ምዕራፍ ከቅዱሳት መጻሕፍት በማንበብና በመጸለይ ሕማሙንና ሞቱን ያዘክራሉ፤ ቅዱስ ያሬድ በመጨረሻው ሳምንት በየዕለቱ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተፈጸመውን ነገረ መስቀል በተመለከተ ያዘጋጀውን መዝሙር ይዘምራሉ፤ አብዝተው ስግደትን ይሰግዳሉ፡፡
Sunday, April 14, 2013
ገብርኄር
በዲ/ን አባተ አስፋ
ዛሬ ታላቁን የጌታችንን ጾም ከጀመርን ስድስተኛ ሳምንት ላይ ደርሰናል፡፡ ይህን ሳምንት ቅድስት ቤተክርስቲያን «ገብርኄር» የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች፡፡ ገብርኄር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ.25-14-30 ነው፡፡
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ መስሎ ካስተማራቸው ትምህርቶች መካከል አንዱ የሆነው ይህ የዛሬው ወንጌል አስተማሪ የሆኑ መሠረታዊ ጉዳዮችን በውስጡ ይዟል፡፡ በተለይ ምንም እንኳን የቤተክርስቲያን ሓላፊነት የእገሌና የእገሊት ተበሎ ባይወሰንም ቤተ ክርስቲያን ባላት የአገልግሎት መዋቅር መሠረት የሓላፊነትን ቦታ ይዘው ለሚያገለግሉ ሰዎች አትኩሮት ሊሰጡባቸው የሚገባቸውን ነጥቦች ይጠቁማል፡፡ ይህን ለማየት ያመቸን ዘንድ ከታሪኩ የመጀመያ ክፍል በመነሣት ዋና ዋና የሆኑ ዐሳቦችን በአትኩሮት መመርመር ጠቃሚ ነው፡፡
Sunday, April 7, 2013
ደብረ ዘይት
በአባ ዘሚካኤል ደሬሳ
የዓለሙ ፍጻሜ ምልክቱ ምንድ ነው?/ማቴ. 24፣3/
በዓቢይ ጾም ውስጥ ካሉት ሳምንታት ደብረ ዘይት 5ኛው ሳምንት ላይ ይውላል፡፡ ደብረ ዘይት ትርጉሙ የወይራ ዛፍ ተራራ ማለት ሲሆን፣ ይህም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም በሚገኘው በደብረ ዘይት ተራራ ቅዱሳን ሐዋርያት” የዓለሙ ፍጻሜስ ምልክቱ ምንድነው?”/ማቴ. 24፣3/ ብለው ጠይቀውት እርሱም የማይቀረውን የዓለም ፍጻሜና አስቀድመው የሚፈጸሙ ምልክቶችን አስረድቷቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ይህንኑ በደብረ ዘይት ሳምንት ታስበዋለች፤ ለምእመናኑም ከዘመኑ ሁኔታ አንጻር በመጻሕፍት የተጠቀሱትን የትንቢት ምልክቶቹን ከተግባራዊ የዓለም ክንዋኔዎች አንጻር በማገናዘብ ታስተምራለች፡፡ በመሆኑም በቤተ ክርስቲያናችን በደብረ ዘይት ሳምንት ምጽአትን አስመልክቶ የሚነገሩ ምስጢራት እጅግ ሰፊ ናቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ ጽሑፍ በመጠኑ የምናየው ከቅዱሳት መጻሕፍት አንጻር በዓለም እየተከሰቱ ካሉ ወቅታዊ ምልክቶች ጋር በማገናዘብ ይሆናል፡፡
Tuesday, March 12, 2013
አርባ መአልትና አርባ ሌሊት ጾመ ማቴ.4፥2
በመ/ር ምሥጢረሥላሴ ማናየ
ይህ ከላይ ያነሣነው ርዕስ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንና አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርባ መአልትና አርባ ሌሊት መጾሙን ያስተምረናል፡፡
በዚህ ኀይለ ቃል ሁለት ታላላቅ ቁም ነገሮችን ቃላትን እንመለከታለን
በዚህ ኀይለ ቃል ሁለት ታላላቅ ቁም ነገሮችን ቃላትን እንመለከታለን
- አርባ መአልትና አርባ ሌሊት
- ጾም የሚሉት ናቸው፡፡
በቅድሚያ አርባ መአልትና አርባ ሌሊት የሚለውን ከእነ ምስጢሩ እንመለከተዋለን፡፡ ቀጥለን ደግሞ ጌታችንስ ለምን አርባ መአልትና አርባ ሌሊት ጾመ? የሚለውን እንመለከታለን እግዚአብሔር አይነልቡናችንን ይክፈትልን፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን የፈጠረውን የሰው ልጆችን አባት አዳምን፣ በልጅነት አክብሮ ገነት ያስገባው በፈጠረው በአርባ ቀኑ ነው፡፡ “ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር ዘገብሮ ለአዳም” አዳምን የፈጠረ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው እያሉ እያመሰገኑ መላእክት ወደገነት አስገብተውታል /ቀሌ.4፥/
Saturday, March 9, 2013
የዐቢይ ጾም ስብከት
በአያሌው ዘኢየሱስ
ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት በሆነችው በቅድስቲቱ ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ጾም እንደ እንግዳ ደራሽ፤እንደ ወንዝም ፈሳሽ በድንገት የተጀመረ ሥርዓተ አይደለም፡፡ በተለይም በአዲስ ኪዳን ዘመን ጾም ሰው ሠራሽ ሕግ ሳይሆን መድኀኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የመጀመሪያ አድርጎ የሠራው ሕግ ነው፡፡ ጌታ በመዋዕለ ስብከቱ በአንድ ወቅት ከመጥምቁ ዮሐንስና ደቀ መዛሙርት ጾምን አስመልክቶ የቀረበለት ጥያቄና የሰጠው መልስ አለ፡፡ ያቀረቡለት ጥያቄ፡- «. . . እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ የምንጦመው፤ ደቀ መዛሙርትህ ግን የማይጦሙት ለምንድር ነው?» (ማቴ 9፡14)
የሚል ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጣቸው መልስ እንዲህ የሚል ነበር፡- «. . . ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን; ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤በዚያን ጊዜም ይጦማሉ፡፡» ማቴ 9፡15፡፡ ጌታ በዚህ መልሱ ውስጥ ራሱን በሙሽራ ደቀ መዛሙርቱንም በሚዜዎች በመመሰል እርሱ በመንፈስ ሳይሆን በሥጋ ከእነርሱ በዕርገቱ ተለይቶ ከመሔዱ በፊት ሊያዝኑ፣ ሊተክዙና ከመባልዕት ሊከለከሉ እንደማይችሉ ነገር ግን በዕርገቱ ሲለያቸው መጾም እንደሚጀምሩ ተናገረ፤አስተማረ፡፡ በመሆኑም «በዚያን ጊዜም ይጦማሉ፡፡» የሚለው ሐረግ እርሱ በገዳመ ቆሮንቶስ የጣለውን የጾም መሠረት እነርሱ ከዕርገቱ በኋላ አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት የሚያጎላ ነው፡፡
|
Subscribe to:
Posts (Atom)