Tuesday, April 8, 2014

ኒቆዲሞስ ዘሠሉስ



በዲ/ን ስመኘው ጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 29 ቀን 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
 የኦሪት ሰንኮፍን ከእኛ ያራቅህልን፣ በሚደነቅ አጠራር ከጨለማ ጠርተህ የዳግም ልደትን የሠጠኸን፣ ሰውነታችን ሳይሆን ነፍሳችን የምትጠራበትን ሕጽበት ምሥጢር የገለጥክልን፣ በሌሊት ጨለማ ሕይወታችን ወደ አንተ እንገሰግሳለን፤ አንተም የጽድቅን የእውነትን ነገር ትገልጥልናለህ:: ከዚያም እውነትህን መመስከር እንጀምራለን:: በመጨረሻም ማንም በሌለበት ወቅት እንኳን ከመስቀልህ ስር ቅዱስ ሥጋህን እንገንዝ ዘንድ እንደ ኒቆዲሞስ ያለፍርሃት በጽድቅና በእውነት እንኖራለን:: ምክንያቱም በአንተ መኖር ያለውን ሰላም ከአይሁድ ተለይተን አይተናልና:: ይህ ሰላምህ ሁልጊዜ አብሮን ይኖር ዘንድ ፈቃድህ ይሁን::

 አብርሃምን በተቀበለበት፣ ይስሃቅን በመረጠበት፣ በሙሴ የዋህነት፣ በሐዋርያት ፍቅር ወደ ቤተክርስቲያን ጠራን፡፡ በረከትን፣ ጸጋን፣ ምሕረትን፣ ተስፋን ሁሉ አደለን” በማለት የዕለቱን ድርሰቱን ይጀምራል:: የተጠራንበት ምሥጢር በሰው ልቡና ታስቦ አይደረስበትም፤ ተመርምሮም አይታወቅም፤ ነገር ግን እንዲሁ የቤተክርስቲያን ልጆች የእርሱም ወዳጆች እንድንሆን ጠራን:: ከዚህ በኋላ እንደ ሁልጊዜው ቤተክርስቲያንን ሰላም ብሎ ያወድሳታል::
  ሥርጉት በስብሐት ቅድስት ቤተክርስቲያንበምሥጋና ያጌጥሽ ቅድስት ቤተክርስቲያን፣ በሰንፔር ዕንቊ በከርከዴን በጳዝዮን ዕንቊዎች ግድግዳዎችሽ ያጌጡ በወርቅ የተለበጡ ናቸው:: አንተ በምሥጋና ዙራት ቤተክርስቲያን ከፍ ከፍ ታደርግሃለች::” “አንቺ ጽዮን ቤተክርስቲያን ሆይ ተነሺ፤ ኃይልሽን ልበሺ፤ ጠላቶችሽን