Saturday, January 11, 2014

ምስጢረ ጥምቀት

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

                        ትምሕርተ ሃይማኖት

ምሥጢረ ጥምቀት
ጥምቀት ማለት ፤ መጠመቅ ፤ መነከር ፤ መደፈቅ ፤ በውሃ ውስጥ ብቅ ጥልቅ ማለት ነው ።
በምሥጢረ ጥምቀት ትምህርታችን:- 
- የጥምቀት ምሳሌዎች ፤
- የጥምቀት አመሠራረት ፤
- በጥምቀት የሚገኝ ጥቅም ፤
- ለጥምቀት የተወሰነ ዕድሜ ፤ የሚሉትን እንማራለን ።
1 የጥምቀት ምሳሌዎች

በብሉይ ኪዳን ዘመን የተፈጸሙና ለአማናዊው የሐዲስ ኪዳን ጥምቀት ምሳሌ ከነበሩት መካከል የሚከተሉትን እናያለን ።

- የጥፋት ውሃ በኖኅ ዘመን በበደላቸው ተጸጽተው ንስሓ ያልገቡ ሰዎችንና (ከኖኅና ቤተሰቡ እንዲሁም ለዘር እንዲቀሩ ከተደረጉት ፍጥረታት በቀር) በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ያጠፋው ማየ አይኅ(የጥፋት ውሃ) የጥምቀት ምሳሌ ሲሆን ፤ ከጥፋት ውሃ የዳኑት ኖኅና ልጆቹ ፤ ከክርስቶስ ጎን ለጥምቀታችን በፈሰሰው ትኩስ ውሃ በጥምቀት ከእግዚአብሔር ተወልደው ከፍርድ ለሚድኑ ምዕመናን ምሳሌ ነው ። ዘፍ 7 ፥ 1 ። ዘፍ ፥ 19 ፡ 1 ። 1ዼጥ 3 ፥ 28 ።
- ግዝረት ዘፍ 17 ፥ 14 ። ግዝረት ለጊዜው ለእስራኤል ዘሥጋ መለያ ሲሆን ፤ ፍጻሜው ግን ሊመጣ ላለውና ለእሥራኤል ዘነፍስ ምዕመናን መክበሪያ ለሆነው ለጥምቀት ምሳሌ ነው ። ቆላ 2 ፥ 14 ።
- የኤርትራ ባህር (ቀይ ባህር) ዘፀ 14 ፥ 21 ። 1ቆሮ 10 ፥ 1 ። ሙ ሴ የክርስቶስ ፤ ባህሩን የከፈለባት በትር የመስቀል ፤ ባህረ ኤርትራ የፍርድና የሲኦል ፤ በተከፈለው ባህር የተሻገሩት እስራኤል በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደሙ  በጥምቀት ከእግዚአ ብሔር ተወልደው ባህረ ኃጢአትን የሚሻገሩ ምዕመናን ምሳሌ ነው ።
- የዮርዳኖስ ባህር ኢያሱ 3 ፥14 ። ኢያ 4 ፥ 15 ። ኢያሱ የክርስቶስ ፤ ዮርዳኖስ የጥምቀት ፤ ይርዳኖስን የተሻገሩ እስራ ኤል በክርስቶስ አምነው በመጠመቅ የዳኑ ምዕመናን ምሳሌ ነው ።
- የዮሐንስ ጥምቀት ማቴ 3 ፥1 ። ዮሐንስ ህዝቡን የንስሓ ጥምቀት እያጠመቃቸው ከቆየ በኋላ ጌታ በሚመጣበት ጊዜ ግን እነሆ የእግዚአብሔር በግ በማለት ወደ ጌታ መርቷቸዋል ስለዚህ የዮሐንስ ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ ለአማናዊዉ የጌታ ጥምቀት የሚያዘጋጅ ነው

የጥምቀት አመሰራረት

ጥምቀትን የመሠረተው ጌታችን ሲሆን ፤ የተጠመቀበትም ምክንያት ።
- በብሉይ ኪዳን ያልተገለጸ አንድነት ሶስትነቱን (ምሥጢረ ሥላሴን) ለመግለጽ ። ማቴ 16 ፥ 17 ።
- እንዴት በማንና የት መጠመቅ እንዳለብን ሊያስተምረን አብነት ሊሆነን ። ዮሐ 13 ፥ 12 ።
- ጠላት ዲያብሎስ በዮርዳኖስ የጣለውን የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ ። ቆላ 2 ፥ 16 ።
 አዳምና ሄዋን ዕፀ በለስን በልተው የአምላካቸውን ትእዛዝ በመተላለፋቸው የተወሰደብንን ልጅነት የምናስመስልበትንና ከእግዚአብሔር የምንወለድበትን አማናዊ ጥምቀት በዮሐንስ እጅ ተጠምቆ ከመሰረተልን በኋላ ፤ በጸሎተ ሐሙስ ማታ የሐዋርያትን እግር በማጠብ አሳይቷቸዋል። ምክንያቱም በዚያ ሰዓት ቅዱስ ዼጥሮስ እኔ አጥብሀለሁ እንጅ አንተ የእኔን እግር አታጥበኝም ብሎ በተከራከረበት ጊዜ ፤ ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር አንድነት የለህም ማለቱ ከእግዚአብሔር አንድ የምንሆንበት በመንፈስ የምንወለድበት ብቸኛው መንገድ ጥምቀት መሆኑን እንረዳለን ።
 ጌታችን ጥምቀትን ከመሠረተልን በኋላ እኛም ከውሃና ከመንፈስ በመወለድ ልጅነትን ተቀብለን መንግስቱን እንደምንወርስ ለኒቆዲሞስ ያስተማረውን እናስታውሳለን ። ዮሐ 3 ፥ 1።
ለሐዋርያትም ሥጢረ ጥምቀት በጸሎተ ሐሙስ ይፈጸምላቸው እንጅ መንፈስ ቅዱስ የወረደላቸው ጌታ በተነሳ በአምሳኛው ፤ ባረገ በአስረኛው ቀን ነው ። ከነሱ በኋላ ምዕመናን ሲጠመቁ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ሲወርድባቸው በግልጽ ይታይ ነበር ። የሐ ሥ  2 ፥ 1 ። የሐ ሥ 8 ፥ 14 ።                             
ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው የተነገረውን ትንቢት የተመሰለውን ምሳሌ ለመፈጸም ነው ።
ምሳሌ
- አብርሐም  የአሕዛብን ነገሥታት ድል አድርጎ ሲመለስ ዮርዳኖስን መሻገሩ ፤ የምዕመናን ጥምቀት መልከ ጼዴቅ የጌታ ምሳሌ ። ዘፍ 14 ፥ 17 ። ዕብ 6 ፥ 1 ።
- እሥራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ርስታቸው ከነዓን መግባታቸው ፤ ምዕመናን አምነው ተጠምቀው ወደ ሰማያዊቷ ርስታቸው መንግስተ ሰማያት የመግባታቸው ምሳሌ ። ኢያ 3 ፥ 14 ።
- ኤልያስ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ማረጉ ፤ ምዕመናን ተጠምቀው ዕርገተ ነፍስ የማግኘታቸው ምሳሌ ። 2ነገ 2 ፥ 8 ።
- ንዕማን  በዮርዳኖስ ተጠምቆ ከለምጽ መዳኑ ፤ ምዕመናን  ተጠምቀው ከነፍስ ለምጽ የመዳናቸው ምሳሌ ። 2ነገ 5 ፥ 14 ።
ትንቢት
ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ ። መዝ 113 ፥ 3 ።
በውሃ የተጠመቀበት ምክንያት
- ውሃ በየትም ቦታ ስለሚገኝ ፤ ሰዎች በቀላሉ ልጅነትን አግኝተው መንግስተ ሰማያት እንዲወርሱ ።
- ውሃ የደረቁ ዕፀዋትን እንደሚያለመልም ፤ ምዕመናን ተጠምቀው ልምላሜ ነፍስ እንዲያገኙ ።
- ውሃ ከእድፍ እንደሚያነጻ ፤ ምዕመናንም ተጠምቀው ከኃጢአት እንዲነጹ ። የሐ 2 ፥ 38 ። ህዝ 36 ፥ 25 ።
- ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋ ፤ ምዕመናንም ተጠምቀው ከገሃነመ እሳት እንዲድኑ ። ማቴ 3 ፥ 6-12 ።
በጥምቀት የሚገኝ ጥቅም
- በምንጠመቅበት ጊዜ በመርገም ከተላለፈብን ኃጢአት ሥርየት እናገኛለን ። ህዝ 36 ፥ 25 ። የሐ 2 ፥ 38 ።
- በጥምቀት ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ስንወለድ ፤ የተወሰደብን ልጅነታችን ይመለስልናል ዮሐ 3 ፥ 1 ።
- ያላመነ ያልተጠመቀ ይፈረድበታል ። ከሚለው የገሃነመ እሳት ፍርድ እንድናለን ። ማር 16 ፥ 16 ።
- በውሃው ስንደፈቅ ከክርስቶስ ጋር የመሞታችን ፤ ከውሃ ስንወጣ የመነሳታችን ምሳሌ ። ሮሜ 6 ፥ 3 ።
- በጥምቀት ከጌታችን ጋር: ገላ 3 ፥ 27 ፤ ከምዕመናን ጋር አንድ እንሆናለን ። ቆላ 2 ፥ 11 ።
ለጥምቀት የተወሰነ ዕድሜ
በሐዋርያት ስብከት ያመኑና በማንኛውም የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሁሉ ይጠመቁ ነበር የሐ ሥራ 16 ፥ 15 ። 1ቆሮ 1 ፥ 15 ። በኋላ ግን ወላጆቻቸው ሊያስተ ምሯቸው ቃል እየገቡ ልጆቻቸውን ወንዶችን በአርባ ሴቶችን በሰማንያ ቀናቸው ማጥመቅ ተጀመረ ።
ለዚህም መሠረቱ

- የእስራኤል ልጆች በተወለዱ ወንድ በአርባ ሴት በሰማንያ ቀናቸው ወላጆቻቸው መባዕ (ስጦታ) ይዘውላቸው ወደ ቤተ መቅደስ እየሄዱ በእስራኤልነት (የዜግነት) መዝገብ እያስመዘገቡ የተስፋዋ ምድር ከነዓን ባለመብቶች (ወራሾች) ያደርጓቸው እንደነበረ ሁሉ ፤ ዛሬም ህጻናት ወላጆቻቸው ሃይማኖታቸውን ሊያስተምሯቸው ሃላፊነት ወስደው የክርስትና አባት ወይም እናት በተጨ ማሪ ቃል ገብተው ክርስትና በመነሳት (በመጠመቅ) የወላጆቻቸውን ርስት መንግስተ ሰማያትን ይወርሳሉ ።
ከአርባ እና ከሰማንያ ቀን በኋላ የሚመጡ ተጠማቂዎች ግን ሃይማኖታቸውን ተምረው ካመኑ በኋላ በማንኛውም የዕድሜ ክልል መጠ መቅ ይችላሉ ። በሕይወት እስካሉ ድረስ መቸም ቢሆን ከመጠመቅ የሚያግዳችው ነገር የለም ።  
አንድ ተጠማቂ የሚያሟላቸው ነገሮች
ከመጠመቁ በፊት ተጠማቂው ሃይማኖቱን በሚገባ ተምሮ ማመንና መመስከር አለበት ። ተጠማቂው ህጻን ከሆነ ወላጆቹ ወይም የክርስታና አባት እናት ቀርበው ሊያስተምሩት ቃል መግባት አለባቸው ።
በሚጠመቅበት ጊዜ በውሃ ውስጥ ሶስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ ማለት አለበት ፤ የክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ምሳሌ ነውና ። ተጠማቂው የሚጠመቀው በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ነው ። ማቴ 28 ፥ 19 ። ተጠማቂዎች ባለትዳሮች ከሆኑና ቤተሰብም ካላቸው ሁሉም ተምረው አምነው በአንድነት መጠመቅ አለባቸው ።
ከተጠመቀ በኋላ መቁረብ (ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል) ይገባል ። ይህ ካልሆነ ጥምቀቱ ህያው አይሆንም ። ቃሉ ሥጋዬን ካልበላችሁ ደሜንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም ይላልና። እያንዳንዱ ለእርሱ ሲል የተቆረሰውን ቅዱስ ሥጋና የፈሰሰውን ክቡር ደም ተቀብሎ ከበደሉ መንጻት አለበት። በጥምቀት የተቀበልነው ልጅነት የሚረጋገጠው ሥጋውንና ደሙን ስንቀበል ብቻ ነውና ።        

ጥምቀት አንዲት ናት ። ኤፌ 4፡5

- ከወላጆቻችን በሥጋ የምንወለደው አንድ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ሁሉ ከውሃና ከመንፈስም ከእግዚአብሔር የምንወለደውም (የምንጠመቀው) አንድ ጊዜ ብቻ ነው ። በመሆኑም ጥምቀት አንዲት ናት አትደገምም ።
- የጥምቀት ምሳሌ የነበረው ግዝረት አንድ ጊዜ ብቻ እንደነበረ ሁሉ ጥምቀትም አንድ ጊዜ ነው ። ቆላ 2 ፥ 11 ።
- ከጌታ ሥጋና ደም የምንሳተፍበት ምሥጢር በመሆኑ ጌታም የሞተውና የተነሳው አንድ ጊዜ ነውና አንድ ጊዜ ብቻ እንጠመ ቃለን ። ሮሜ 6 ፥ 3 ። በእኛ ቤተ ክርስቲያን ከተጠመቀ በኋላ በሌላ ሃይማኖት ገብቶ እንደገና ቢጠመቅ ወይም ከሌላ እምነት ተከታይ ጋር ጋብቻ ቢመሠርት በንስሓ ከተመለሰ በኋላ መጽሐፈ ቄድር ተጸልዮለት ይጠመቃል ። ይህ ግን ሁለተኛ ጥምቀት ሳይሆን የንስሓ ጥምቀት ይባላል ።
ከኦርቶዶክሳውያን ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት (Oriental Churches) በቀር በሌላ ማንኛውም ቤተ ክርስቲያን ከተጠመቀ በኋላ አምኖ የሚመጣ ሰው ቢኖር እንደገና ይጠመቃል ።

Saturday, January 4, 2014

ስለ ገና በዓል እና ጾም አንዳንድ ጥያቄዎች


የገና እና የጥምቀት በዓላት ሲደርሱ በምእመናኑ ዘወትር የሚጠየቁ ጥያቄዎች አሉ፡፡ እነዚህን እና መሰል የሕዝቡን የዘወትር ጥያቄዎች መልስ የያዘ የማያዳግም ጥራዝ ማውጣት ከሊቃውንት ጉባኤ የሚጠበቅ ነው፡፡ አብዛኞቹ ጉዳዮች አበው ቀድመው ሥርዓት የሠሩባቸው እና ማብራርያ ብቻ የሚያስፈልጋቸው ናቸውና፡፡ ለዛሬ ሦስቱን ብቻ እንመልስ፡፡

ገና እና ጥምቀት ዓርብ እና ረቡዕ ቢውሉ ይበላባቸዋል ወይስ ይጾማሉ?

ፍትሐ ነገሥት፡ ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር /ዐንቀጽ 15፣ ቁ566/

የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ /ዐንቀጽ 15፣ቁ 603/

የገና እና የጥምቀት ቅዳሴ ስንት ሰዓት ነው?

ፍትሐ ነገሥት፡ ስለ ልደት እና ጥምቀት ግን በዚያ ዘመን በኒቂያ የተሰበሰቡ ሊቃውንት ቅዳሴው በሌሊት ይሆን ዘንድ አዘዙ /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 595/

ልደት ጋድ አለው?

ፍትሐ ነገሥት፡ የልደት እና የጥምቀት በዓላት ጋድ አላቸው /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 566/

     ትንታኔ፡ የገና ጾም 44 ቀናትን ይይዛል፡፡

                   40 ጾመ ነቢያት

                     3 ጾመ አብርሃም ሶርያዊ

                    1 ጋድ

               ድምር 44

የገና ጋድ ከጾሙ ተያይዞ የተቀመጠ እንጂ ለብቻው የተቀመጠ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ሰሙነ ሕማማት ለብቻው የሚቆጠር ጾም ነው፡፡ /ዐንቀጽ 15፣ቁ 565/ ነገር ግን አንድ ሰው ዐቢይ ጾምን ሳይጾም ከርሞ ሕማማትን ለብቻው መጾም አይችልም፡፡ የገናም ጋድ እንዲሁ ነው፡፡

ይህንን ጋድ የልደትን ጾም የማይጾሙ ሰዎች እንዲጾሙት የተሠራ ነውን?

መልስ፡ በቤተ ክርስቲያን ላልተጠመቁ፣ ለማይቆርቡ፣ ንስሐ ለማይገቡ፣ ለማያስቀድሱ፣ ለማይጾሙ ሰዎች ተብሎ የተሠራ ልዩ ሥርዓት የለም፡፡ በፍትሐ ነገሥት ዐንቀጽ 15፣ ቁ 565 እንደተገለጠው ሰባቱ አጽዋማት «ለክርስቲያን ሁሉ» የታዘዙ ናቸው፡፡ ስለዚህም የገናን ጾም ክርስቲያን ሁሉ ጾመው በበዓለ ልደት ሊገድፉ ይገባቸዋል፡፡ ፍትሐ ነገሥት ስለ ገና ጾም ሲገልጥ «መጀመርያው የኅዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል ነው» ይላል /ዐንቀጽ 15፣ ቁ 568/፡፡ ይህም ከገና ጾም ተሸርፎ የሚጾም ነገር እንደሌለው ያሳያል፡፡

መልካም በዓል

Wednesday, November 13, 2013

ጽድቅን መከተል

ጽድቅ እያንዳንዱ ሰው ወደ ክርስቲያናዊ ፍጹምነት በሚያደርገው ጉዞ ሊያፈራው የሚገባ ፍሬ ነው፡፡ ‹‹መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።›› (ማቴ.፫÷፲) ጌታችን ስለ እነዚህ ፍሬዎች ጥቅም የነገረንም ይህንኑ ነው፡፡ ከመቀጠላችንም በፊት ጌታችን የነገረንን ተጨማሪ ነገር እንስማ ፡-‹‹በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም። እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።›› (ዮሐ. ፭÷፬—፭) እናም ፍሬን ለማፍራት የመጀመሪያው መመሪያ ይህ ነው፡፡ ‹‹ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም፡፡›› ማንም ሰው በራሱ ጥረት ብቻ ሊያፈራ አይችልም፡፡ ፍሬያማዎች የሚያደርገን እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡

እግዚአብሔር መሬት እንዳለውና መሬቱን እንዲንከባከቡ አገልጋዮችን እንደቀጠረ ገበሬ ነው፡፡ መሬቱና ዘሩ የእግዚአብሔር ነው ፤ ማዳበሪያውም እንዲሁ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለእርሻ የሚያስፈልገውን ዝናምና ፀሐይም ያዘጋጃል፡፡ የተቀጠረው አገልጋይ ደግሞ በሚገባ ማረስ ፣ ዘርን መዝራት ፣ አረምን ማረም ፣ ማዳበሪያን ማድረግና የድካሙን ዋጋ ማጨድ ይጠበቅበታል፡፡ ነገር ግን የቅጥረኛው ሠራተኛ ሥራውን ከመሥራት በስተቀር በሠራው ነገር ላይ መብት የለውም፡፡ በእኛም እንዲሁ ነው ‹‹እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ። የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፥ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ።›› እንዳለን ጌታችን፡፡ (ሉቃ. ፲፯÷፲)

ቅድስና እንዲሁ አይከሰትም፡፡ አንድ ሰው በተገቢው መንገድ ቅድስናን ለማግኘት መለማመድ አለበት፡፡ አንዳንድ ጊዜ በጎነት ከምድር እስከ ሰማይ በሚደርስና ብዙ ደረጃዎች ባለው መሰላል ይመሰላል፡፡ አንዳንድ በጎነቶች በመሰላሉ ከሥር ሲገኙ ሌሎች ደግሞ
ከመሰላሉ ጫፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ አባቶች እነዚህን መሰላሎች ዘልለን ልናልፋቸው አንችልም ነገር ግን ደረጃ በደረጃ ልንወጣቸው ይገባናል ይላሉ፡፡ በታችኛው የመሰላሉ መውጫ ላይ ሁለት መሠረታዊ የሆኑ የጽድቅ ሥራዎች አሉ፡፡ እነዚህም መታዘዝና ትእግሥት ናቸው፡፡
በመሰላሉ የላይኛው ጫፍ ላይ ደግሞ ትሕትናና ፍቅር አሉ፡፡ ፍቅር ከሁሉም የበጎነት ደረጃዎች ከፍተኛው ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜም ‹ሁሉን የሚያጠቃልል በጎነት› ተብሎ ይጠራል፡፡

ፍቅር ያለው ሁሉም በጎነቶች ይኖሩታል፡፡ በጎነትን ስንለማመድ አንድ በአንድ ልንለምዳቸው እንደሚገባን ይመከራል፡፡ አንዱን የበጎነት ደረጃ ተለማምደን ስንጨርስ የመሰላሉን ቀጣይ ደረጃ ደግሞ እንወጣለን፡፡ በጎነት በየጊዜው እየዳበረ የሚሔድ ነገር ነው፡፡ አንዱን
በጎነት መልመድ የሚቀጥለውን በጎነት በቀላሉ ለማግኘት ያስችላል፡፡ ለምሳሌ ራስህን ትእግሥትንና መታዘዝን ካስለመድኸው የዋህነትም የአንተ ይሆናል፡፡ የዋህነትን ስትይዝ ደግሞ በትሕትና ደጃፍ ላይ ነህ እንዲህ እያለ ይቀጥላል፡፡

አንድ ልምምድ አለማማጅ ወይም አሰልጣኝ ይፈልጋል፡፡ ማንም ሰው ያለ አሰልጣኝ በአትሌቲክስ ሊሳካለት አይችልም፡፡ እንዲሁም አንድ ክርስቲያን ያለ አሰልጣኝ ‹የክርስቶስ /መንፈሳዊ/ ሯጭ› ሊሆን አይችልም፡፡ አሰልጣኝህ ደግሞ የንስሐ አባትህ ናቸው፡፡ በልምምድህ ወቅትም ትእዛዝ ሊሰጡህ የሚገባው እርሳቸው ናቸው፡፡ ያለፈውን ምእራፍ አንብበኸውና ተረድተኸው ከሆነ በእርግጠኝነት ይህን ልምምድ በራስህ የማድረግህን አደጋ ትረዳዋለህ፡፡ ታዛዥነትና ትእግሥት ሌሎች በጎነቶችን ለማግኘት እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህን መሠረታዊ በጎነቶች ካልያዝህ ሌሎች የበጎነት ፍሬዎችን ልታፈራ አትችልም፡፡ የዚህም ምክንያቱ ታዛዥ ካልሆንህ በአሰልጣኝህ /በንስሐ አባትህ/ የሚሰጥህን ትእዛዝ ልትፈጽም አትችልም፡፡ በእርግጥም ምንም ዓይነት እድገት አይኖርህም፡፡ እንዲሁም ትእግሥት ሳይኖርህ ልምምድህን በጽናት ለማካሔድና ፍሬ ለማፍራት አትችልም፡፡ በዘር ዘሪው ምሳሌ ላይ ጌታችን እንዲህ ሲል ነግሮናል ፡- ‹‹በመልካም መሬት ላይም የወደቀ እነርሱ በመልካምና በበጎ ልብ ቃሉን ሰምተው የሚጠብቁት በመጽናትም ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።››
(ሉቃ. ፰÷፲፭)

ምንጭ ተግባራዊ ክርስትና
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንደተረጎመው
መጽሐፉን በነጻ እዚህ ያግኙ

The Supreme Importance of Churchmanship in an Age of Radical Individualism by Saint John Chrysostom


February 5, 2013 at 2:33pm

The Supreme Importance of Churchmanship in an Age of Radical Individualism by Saint John Chrysostom from an article Saint John Chrysostom and 21st Century Christians (I dedicate this especially for those living in atmosphere of INDIVIDUALISM, please read through you shall see your self inside)

Saint John taught that the κοινωνοία (communion by intimate participation) of the Church is a profound miracle. When is the origin of the Church? From where did our sacred community arise, brothers and sisters? It has no mere human foundation. The apostles did not simply gather together and come up with the idea of this organization, with certain goals, members, and dues. Not at all! The Church is the continuation of the miracle of the Nativity of Christ. The Son of God was enfleshed in the womb of the Holy Virgin, and born into the world. The Son of God is progressively enfleshed in the establishment and propagation of the Church in the world. The Church is His very Body, the miraculous expansion of His Incarnation in the world. The supernatural origin of the Church is demonstrated, according to St John Chrysostom, by the miracle that took place on the Precious and Life-Giving Cross. When our Savior was hanging upon the Cross He was pierced with a spear, and suddenly blood and water poured out from His sacred side. This blood and water is Holy Baptism by which one is incorporated into the Church, and the Holy Eucharist by which one grows in the Church. These holy mysteries came forth from the side of our Savior in the same way that Eve was taken from the side of Adam. The Church is the Bride of Christ, and so was taken from His side while on the Cross as a fruit of His sacred atonement. She is a miracle of new creation.

Our unity in the Church, according to Chrysostom, is a supernatural wonder. In the Church we experience an intimate union with Jesus Christ. This reality of being “in Christ” is the most used image by the great Apostle Paul in describing the Christian life. The Christian life is a Church life, for it is by Holy Baptism that we are incorporated into Christ and His Church. As Christians we possess a unity far greater than that of earthly organizations. We share a common womb, a common mother in the Church, a common Father in God, a common table from which we eat our food of everlasting life, a common language of doxology, a common quest, a common animating spirit, a common ethic, and a common destiny. This unity is expressed each Divine Liturgy, according to Saint John Chrysostom, in our partaking of the Holy Eucharist in which partaking we are actualized together as the Body of Christ. This is the reason that we celebrate the Holy Liturgy with one single holy chalice. The singular sacred cup bears witness to our unity. Even should we distribute Holy Communion in multiple chalices we do not bless multiple chalices. We consecrate one alone, and then we bring other empty chalices and fill them from the one sacred chalice.

Our experience of Church is transformative. The sacredness of our community is testified to by what actually happens when we gather together around the holy altar. Divine services are the single most powerful agent in personal holiness. “Nothing contributes to a virtuous and moral way of life as does the time you spend here in church.” There is grace behind every action of the Holy Liturgy. Chrysostom often waxes eloquent concerning the liturgical movements of the service. When the deacon exclaims “Stand upright,” he is addressing our souls primarily, and not just our bodies. The preaching sanctifies. The Holy Eucharist enlivens and flames leap from our mouths, blood is painted on the doorposts of our bodies and the angel of death passes over us. Nothing is more precious, more central, more transformative and miraculous, in our human existence than life in the Church.

With the gift of this sacred community come sacred obligations to every Christian. True sacred fellowship is the power of the Church. Listen to the words of Chrysostom, “Let us prefer the time we spend here in church to any occupation or concern. Tell me this. What profit do you gain which can outweigh the loss you bring on yourself and your whole household when you stay away from the religious services? Suppose you find a whole treasure house full of gold, and this discovery is your reason for staying away. You have lost more than you found, and your loss is as much greater as things of the spirit are better than things we see. Attendance in the divine services greatly encourages your brothers and sisters in the faith and spiritual battle ... the Church went from 11 to 120 to three thousand to five thousand to the whole world and the reason for this growth was that they never left their gathering. They were constantly with each other, spending the whole day in the temple, and turning their attention to prayers and sacred readings. This is why they kindled a great fire. We too must imitate them.”
Chrysostom taught that the communal responsibilities of Christian people far exceeded their merely needing to be faithful participants in the divine services. He called upon them to take responsibility for each other, and to function as an authentic family. If a faithful Christian is friends with a lazy Christian, the faithful one should go to the lazy one on Sunday, and literally drag him along to liturgy. While commenting on Psalm 50 Chrysostom stated that if an immoral Christian was seen by other congregants getting into the communion line the faithful should report this immediately to the priest so he can exclude him from communion. If a faithful Christian hears his brother blaspheme he should strike him in the mouth, and “sanctify his right hand.” The picture of communal responsibility is clear, and in our individualistic live-and-let-live context, appears extreme. But Chrysostom holds membership in the Church very high and assumes that there are many communal responsibilities associated with it designed by a loving God to work for the salvation of the entire community. And the responsibilities do not lie solely with the laity. The clergy must be serious pastors. They must not leave their sheep diseased or in danger. An example of such serious pastoring can be found in Chrysostom’s own life as a priest at the time of the tax riots in Antioch. Saint John preached a series of 21 sermons during the tense days following the riots. During this series Chrysostom sought to reform his people from the habit of swearing. No less than 15 times did Saint John address the subject in a period of just a few weeks, sermon after sermon. He knew his people were growing very weary of him preaching with the same focus, yet they had not ceased their bad habit and Chrysostom refused to pretend that they had and move on. Finally, he acknowledged their grievances and assured them that he could move on very quickly if they wished. They only needed to stop swearing and then he would move on. It was completely in their hands. He was a faithful physician, and not a professional or a show-man. He insisted on bettering his patients. The result was that swearing decreased and Chrysostom moved on, but a most important point about life in the Church had been expressed by the Saint. The life we lead in the Church is a life centered on personal change.

Brother and sisters, many of our Orthodox people do not have an authentic experience of what true ecclesial life is. We do not appreciate the miracle of life in the Church, and we content ourselves with an empty and alienating individualism. An evil spirit of “it’s just me and Jesus, baby” has permeated much of American Christianity today to our nation’s detriment. Our faith teaches us that there is no dichotomy between Jesus and the Church. Our Savior is not a floating head to be communed with apart from His sacred Body. Churchmanship is at an astonishing low in our times. Saint John Chrysostom stands at the throne of God ready to illumine us and our people about the miracle of sacred community, and to save us from the death of self-worship. This age of individualism and religious game playing is a time for serious pastoring, revived churchmanship, and sacred obedience to the Church. May the God Bless us all!

Monday, October 14, 2013

ጸሎት


መጋቢት 18/2004 ዓ.ም.
በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ
ጸሎት ጸለየ፡- ለመነ፣ ጠየቀ አማለደ፣ ማለደ ካለው የግዕዝ ቃል የወጣ ቃል ነው፡፡ ጸሎት ማለት ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር እግዚአብሔርን ማመስገን መለመን፣ መጠየቅ፣ መማለድ፣ መማፀን ነው፡፡ “ጸሎት ብሂል ተናግሮ ምስለ እግዚአብሔር፡፡” አባታችን አዳምም ከመላእክት ተምሮ በየሰዓቱ ይጸልይ ያመሰግን ነበር፡፡ ዲያብሎስ በእባብ አድሮ ወደ አዳም በመጣ ጊዜ ጸሎት እያደረገ ስለነበር ዲያብሎስን ድል ነሥቶታል ሔዋንን ግን ሥራ ፈትታ እግሯን ዘርግታ ስለአገኛት ድል ነስቷታል፡፡
ጸሎት ሰማእታት ከነደደ እሳት፣ ከተሳለ ስለት፣ ከአላውያን መኳንንት፣ ከአሕዛብ ነገሥታት ከዲያብሎስ ተንኮል እና ሽንገላ ዲያብሎስ በእነርሱ ላይ ከአጠመደው አሽከላ የዳኑበት ጋሻ ነው፡፡ ኤፌ.6፥10 21 ጸሎት፣ ሰው አሳቡን ለእግዚአብሔር የሚገልጥበት እግዚአብሔርም የሰውን ልመና ተቀብሎ ፈቃዱን የሚፈጽምበት ረቂቅ ምስጢር ነው፡፡
የጸሎት መሠረቱ “ዕሹ ታገኛላችሁ ለምኑ ይሰጣችኋል ደጁ ምቱ ይከፈትላችኋል” የሚለው የጌታችን ትምህርት ነው ማቴ.7፥7
ጸሎት፡- በሦስት ክፍል ይከፈላል
  1. ጸሎተ አኰቴት
  2. ጸሎተ ምህላ
  3. ጸሎተ አስተብቊዖት
  1. ጸሎተ አኰቴት፡- ማለት እግዚአብሔርን ከሁሉም አስቀድሞ ስለተደረገልን ነገር በማመስገን የሚጀመር ጸሎት ነው ይህም ዓይነት ጸሎት የቅዱስ ባስልዮስን የምስጋና ጸሎት የመሰለ ነው፡፡
“ነአኲቶ ለገባሬ ሠናያት ላዕሌነ እግዚአብሔር መሐሪ”
“ለእኛ በጎ ነገርን ያደረገ ይቅርባይ እግዚአብሔር አምላካችንን እናመሰግነዋለን” ይልና ምክንኀያቱን ሲገልጥ ጠብቆናልና፥ አቅርቦናልና፥ ወደ እርሱም ተቀብሎናልና፥ እስከዚችም ሰዓት አድርሶናልና” ይላል፡፡ /ሥርዐተ ቅዳሴ/ ይህ ጸሎት የምስጋና ጸሎት /ጸሎተ አኰቴት/ ይባላል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን የምስጋና ጸሎት ለፊልጵስዮስ ክርስቲያኖች ሲጽፍላቸው “ነገር ግን በሁሉ ነገር ጸልዩ ማልዱም እያመሰገናችሁም ልመናችሁን ለእግዚአብሔር ግለጡ” ይላል፡፡ ፊል.4፥6 ዳግመኛም “ስለእናንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ ስለተሰጣችሁ ጸጋ ዘወትር እግዚአብሔርን አመስግነዋለሁ” 1ቆሮ.1፥4 ብሎ ከመለመን አስቀድሞ እግዚአብሔርን ማመስገን አስፈላጊ መሆኑን አስተምሯል፡፡ በዚህ መሠረት ሰው የተደረገለትን በጎ ነገር ሁሉ በማሰብ ፈጣሪውን ማመስገን ከማመስገንም ቀጥሎ የሚያስፈልገውን ከፈጣሪው መለመን አስፈላጊ ነው፡፡
ከቅዱስ ጳውሎስ የምንማረው ለእኛ ስለተደረገልን ብቻ ማመስገንን አይደለም፤ ሌሎች ስለተደረገላቸውም ማመስገን ተገቢ መሆኑን እንጂ፡፡ “ለእናንተ ስለተሰጣችሁ ጸጋ ዘወትር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” ሲል ለወገኖቹ ስለተደረገላቸው በጎ ነገር በደስታ ማመስገኑ ነው፡፡ ክርስትና ማለት ለእኔ ብቻ ማለት ሳይሆን ለሌሎችም መኖር፣ ለሌሎች በተደረገው የእግዚአብሔር ስጦታም ደስ መሰኘት ነው፡፡ ይህን የምስጋና ጸሎት /ጸሎተ አኮቴት/ ብዙ አባቶች፣ እናቶች ተጠቅመውበታል፡፡ ለምሳሌም ያህል ዘካርያስንና ኤልሳቤጥን መመልከት እንችላለን፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥ እግዚአብሔር ያደረገላትን በጎ ነገር ስትመሰክር “እግዚአብሔር በዚህ ወራት ከሰው ስድቤን ያርቅ ዘንድ በጎበኘን ጊዜ እንዲህ አደረገልኝ” ብላለች፡፡ ሉቃ.1፥25 እግዚአብሔር ጎበኘኝ ብላ ቸርነቱን አደረገለኝም በማለት የተደረገላትን መልካም ስጦታ ዮሐንስን መጽነሷን ገልጣ አመስግናለች፡፡ ዘካርያስም እንዲሁ አመስግኗል፡፡ “ያን ጊዜም አፉ ተከፈተ አንደበቱም ተናገረ እግዚአብሔርንም አመሰገነ” ሉቃ.1፥65 “ከዚህ ጊዜ ያደረስከኝ፥ ከደዌ የፈወስከኝ፥ ዮሐንስን የሰጠኸኝ ብሎ ፈጣሪውን አመስግኗል በመቀጠልም ይቅር ያለን ለወገኖቹም ድኅነትን ያደረገ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን ከባሪያው ከዳዊት ቤት የምንድንበትን ቀንድ አስነሣልን፡፡” ሉቃ.1፥68 በዘካርያስ ጸሎት ውስጥ ምስጋናውን አስቀድሞ ትንቢቱን አስከትሎ እናገኘዋለን፡፡ በዚህ ምስጋናውና ትንቢቱ አምላክ ለእኛ ያደረገው የቤዛነቱን ሥራ በመግለጥ ሲያመሰግን እንመለከታለን፡፡
2. ጸሎተ ምህላ፡- ጸሎተ ምህላ ስለፈውሰ ሕሙማን …… ስለ ሀገርና ስለነገሥታት ስለ ጳጳሳት፣ ካህናት ዲያቆናት፣ ምዕመናን ሕይወት ቸነፈር፣ ጦርነት፣ ረሀብ፣ ድርቅ ወይም ሌላ አስጊ ነገር በሆነ ጊዜ በብዛት፣ በማኅበር የሚጸለይ ጸሎት ነው፡፡ የምህላ ጸሎት ሲጸለይ በእስራኤል ላይ ቸነፈር በተነሣ ጊዜ አሮን በሽተኞን ባንድ ወገን ጤነኞችን ባንድ ወገን አድርጎ የክህነት ልብሱን ለብሶ ማዕጠንተ ወርቁን ይዞ በራስህ የማልክላቸውን አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብን አስበህ የወገኖችህን ኀጢአት ይቅር በል”  እንደጸለየላቸው ነው፡፡ ዘኁ.16፥46-50

ዛሬም ካህናት ከጠቀስናቸው አስጊ ነገሮች ማንኛውም በሀገር ላይ ቢመጣ ወደ ሀገር እንዳይገባ ገብቶ ቢሆን ከፍ ያለ ጉዳት እንዳያመጣ የክህነት ልብስ ለብሰው ማዕጠንቱ ይዘው ሥዕለ ማርያም፣ መስቀል አቅርበው ማኅበረ ክርስቲያንን ሰብስበው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን “ስለእኛ ከድንግል ማርያም መወለድህን ስለእኛ መሠቀል መሞትህን አስበህ የህዝብን ኀጢአት ይቅር በል ከመዓት ወደ ምሕረት ተመለሰ” እያሉ በምህላ ይጸልያሉ፡፡

የምህላ ጸሎት መአትን መቅሰፍትን ይመልሳል ጦርን፣ ቸነፈርን ያስታግሳል መሠረቱም፡፡
“ጾም ለዩ ምህላ ስበኩ” ያለው ቃል ነው፡፡ ይህ ጸሎት በሰላም ጊዜ ሰላሙ ዘላቂ እንዲሆን በጦርነት ጊዜ ለመከላከያነት ዋና መሣሪያ ነው፡፡ ስለዚህ አጥብቀን ልንከተለው ይገባል፡፡

የምህላ ጸሎት ነገሠታት ከዙፋናቸው ወርደው ወንድ ሙሽራ ሴት ሙሽራ ከጫጉላቸው፣ ከመጋረጃቸው ለምግብ የደረሱ ልጆች ከምግብ ለምግብ ያልደረሱ ከጡት ተከልክለው ሕዝብ ሁሉ ምንጣፍ ለብሰው አመድ ነስንሰው የሚጸልዩት ከፍተኛ ጸሎት ነው ኢዩ.2፥12-18፣ ዮና.3፥5

3.    ጸሎተ አስብቊዖት
ይህ ጸሎት አንድ ሰው ስለሚፈልገው ነገር ቦታ ለይቶ ሱባኤ ገብቶ የሚጸልየው ጸሎት ነው፡፡ ይህ ጸሎት በተለይ ጣዕመ ጸጋን በቀመሱ በተባሕትዎ፣ በምናኔ በገዳም በሚኖሩ አበው ዘንድ የተለመደና የሚደረግ ጸሎት ነው፡፡ ወጣንያን እግዚአብሔርን ጠይቀው አድርግ አታድርግ የሚል መልስን አይጠብቁም፡፡ ፍጹማን አባቶች ግን እግዚአብሔር ጠይቀው አድርግ ወይም አታድርግ የሚል ፈቃደ እግዚአብሔርን ሳይቀበሉ የሚያደርጉት ነገር የለምና ቦታ፣ ጊዜ ወስነው ፈቃደ እግዚአብሔር ይጠይቃሉ፡፡ ይህ ጸሎተ አስተብቊዖት ይባላል፡፡ ይህም ማለት መላልሶ ደጋግሞ ያለ ዕረፍት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚደረግ ጸሎት ነው፡፡ ለምሳሌ ትልቁ መቃርስ ዓለምን ዞሮ ለመጎብኘት ለተከታታይ አምስት ዓመታት እግዚአብሔርን ከለመነ በኋላ እየዞረ መካነ ቅዱሳንን እንዲጎበኝ ከእግዚአብሔር ፈቃድ አግኝቷል በዚህም ከእርሱ ከገድል በትሩፋት የሚበልጡ መናንያን በማግኘቱ መነኮሳትማ እነርሱ እንጂ እኔ ምንድን ነኝ? እያለ ራሱን እየወቀሰ እንደተመለሰ በመጽሐፈ መነኮሳት ተጽፎ እናገኛለን፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን “መስተበቊዕ” የሚባል የጸሎት ክፍል፡፡ አለ ይህ ጸሎት በካህናት አባቶቻችን ስለሙታን፣ ስለሕያዋን፣ ስለነገሠታት፣ ስለ ጳጳሳት ስለ ንዑሰ ክርስቲያን፣ ስለ ምእመናን መባዕ ስለሚያቀርቡ ስለነጋድያን፣ ስለዝናም ስለ ወንዞች የሚጸለይ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የጸሎት ክፍል ነው፡፡

ጠቅላላውን በቤተ ክርስቲያን የሚጸልዩ ጸሎታት ጸሎተ ፍትሐት፣ ጸሎተ ተክሊል፣ ጸሎተ ህሙማን፣ ጸሎተ ቅዳሴ፣ ጸሎተ ሰዓታት፣ የግል ጸሎት፣ የማኅበር ጸሎት እነዚህ ሁሉ ከላይ ከዘረዘርዓቸው ሦስቱ የጸሎት ክፍሎች አይወጡም፡፡ ከጸሎተ አኰቴት ከጸሎተ ምህላ፣ ከጸሎተ አስተበቊዖት ይመደባሉ፡፡ እነዚህን ጸሎታት በሰቂለ ኅሊና በአንቃዕድዎ /ዐይንን ወደ እግዚአብሔር በማንሳት/ መጸለይ ታላቅ ዋጋ የሚያሰጥ ከሰይጣን ወጥመድ የሚታደግ ሕይወትን የሚስተካከል ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቅ አጋንንትን የሚያርቅ ኀይለ እግዚአብሔርን ለሚጸልየው የሚያስታጥቅ መላእክትን የሚያስመስል ነው፡፡

እኛም ሰውነታችን ከበደል ልቡናችን ከቂም ከበቀል እንዲሁም ከተንኮል ንጹሕ አድርገን ብንጸልይ እንጠቀማለን ጸሎታችን ተሰሚ ልመናችንና ጩኸታችን ግዳጅ ፈጻሚ ይሆናል፡፡ የአባቶቻችን ጸሎት የተቀበለ እግዚአብሔር አምላካችን ጸሎታችንን ይቀበለናል፡፡

ይቆየን

Wednesday, September 4, 2013

የዘመን አቆጣጠር ባሕረ ሐሳብ

Source: Dn. Melaku Ezezew

1. ባሕረ ሐሳብ ማለት ምን ማለት ነው?

ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽም የሐሳብባሕር ማለት ነው፡፡ በዓላት እና አጽዋማትን ለማውጣት የመደመር፣ የመቀነስ፣የማባዛት ስሌትን ብቻ ሳይሆን ሐሳበ ፀሐይን፣ ሐሳበ ወርኅን፣ ሐሳበ ከዋክብትን ሐሳበዐበቅቴን ወዘተ አጠቃሎ የያዘ እንደ ባሕር የሰፋ በመሆኑ የሐሳብ ባሕር ተብሏል፡፡የዘመን አቈጣጠር ማለት ስለማሕበራዊ ኑሮ ጠቄሜታና የሃይማኖት ተግባሮችለማከናወን በሚያገለግል መልኩ ተፈጥሮአዊውን የወቅቶች ክፍፍል እርስ በርሳቸውየማመቻቸት ዘዴ ነው፡፡
ማርቆስ ወንጌላዊ

ሐሳበ ዘመን የዘመን አቆጣጠርማለት ሲሆን የሐሳበ ዘመን ትምህርትባሕረ ሐሳብ ይባላል፡፡ ባሕረ ሐሳብየሚለው ቃል ሐሰበ ቆጠረ ከሚለው ግስየወጣ ዘመድ ዘር ነው፡፡ ስለዚህ ባሕረሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ወይምዓመተ ዓለም ማለት ነው፡፡ ባሕረሐሳብ መባሉም የባሕር አዝዋሪቱ፣መንገዱን፣ ጥልቀቱና ስፋቱ ረዥምናሰፊ እንደሆነ የባሕረ ሐሳብ ትምህርትምመንገዱን ስፋቱ ልዩ ልዩ በሆነየአጽዋማትና የሱባዔያት ምሥጢርየተሰናዳ ስለሆነ ነው፡፡