በዲ/ንስመኘውጌትዬ
(መቅረዝ ዘተዋሕዶ፣ መጋቢት 8
ቀን፣ 2006 ዓ.ም.)፡- በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
በአብና በወልድ
በመንፈስ
ቅዱሥ
ስም፣
አንድ
የናዝራውያን
አምላክ፣
የማይለወጥ
የሃይማኖት
ምሰሶ፣
የማይፍገመገም
የመርከባችን
አለቃ፣
የማይጨልም
የፋናችን
ብርሃን፣
ከዘመናት
አስቀድሞ
በህልውና
አንድ
የሆነ፣
በስምና
በስልጣን
የሰለጠነ፣
የመለኮቱ
አንድነት
በማይለወጥ፣
የመንግስቱ
ስፋት
በማይወሰን፣
የብልጥግናው
ክብደት
በማይለካ፣
በአንዱ
በእርሱ
ስም
ሰላም
ይደረግልን፡፡
በጠዋት
ተነስተን
ለነፍሳችን
የሚሆን
ቁርስ
ፍለጋ
“እምነ
ጽዮን
በሀ
ቅድስት
ቤተክርስቲያን
ሥርጉት
በስብሐት
አረፋቲሃ
ዘመረግድ…
እናታችን
ጽዮን
ቤተክርስቲያን
ሰላም
ላንቺ
ይሁን፡፡
ቅድስት
ቤተክርስቲያን
መሠረቶቿ
መረግድ
ናቸው::
በምስጋና
ተሸልማለች፡፡
አዳራሿም
በቢረሌ::
ከሰማዕታት
ከገድላቸው
ጽናት
የታላቁ
ንጉሥ
የሕግ
ታቦት
መሠረትሽ
የእውነት
ፀሐይ
ያበራልሻል::”
ሰው
የሥጋውን
እንቅልፍ
ሲጨርስ
ከሁሉ
አስቀድሞ
ለነፍሱ
ሰላምን
ያገኝ
ዘንድ
የወለደችው
እናቱን
ሰላም
ይላታል::
እንደ
እናታችን
ያማረ
ውብ
የለም::
ስለዚህ
በዚህች
ውብ
ፊት
ለነገ
ስንቅ
የሚሆነንን
ሃብት
በጠዋት
እንደ
ጎበዝ
ገበሬ
እናዘጋጃለን::
እርሷን
እያየን
የሚመጣውን
ቤታችንን
በእርሷ
አምሣል
እንገነባለን::
ወደዚያች
ቤት
መቼ
እንደምንሄድ
ባናውቅም::
ስለዚህ
ሊቁ
እንዲህ
ይለናል፡-
“ድልዋኒክሙ
ንበሩ
እስመ
ኢተአምሩ
ጊዜ
ዘይመጽዕ…
ባለቤት
የሚመጣበትን
አታውቁምና
ተዘጋጅታችሁ
ኑሩ::
በሠርክ
ቢሆን፣
በመንፈቀ
ሌሊት
ቢሆን፣
በጧት
ቢሆን
አታውቁምና
ተዘጋጅታችሁ
ኑሩ::”
አቤቱ
የንጥቂያ
ሠዓት
መቼ
እንደሆነ
አናውቀውምና
በጨለማ
ሳለን
አትውሰደን::
“መራሕከነ
በጸጋከ
ውስተ
ሕይወት…
በጸጋህ
ከጨለማ
አውጥተህ
ወደ
ሕይወት
መራኸን::
የክብር
ምሥጋና
የመንግስት
ጌጥ
የሞት
ስልጣኑ
በመስቀል
ተሸነፈ::”
በእኛ
ችሎታ
ሳይሆን
ዘለዓለማዊ
ሕይወት
የምንወርስበትን
ልምምድ
በጠዋት
አንስተህ
ወደቤትህ
እንድንገሠግሥ
በማድረግ
የምሥጋና
ወታደሮች
አደረግኸን::
ስለዚህም
“ነአኩተከ
አበ
ልዑላን
ዘትነብር
መልዕልተ
አርያም…
በአርያም
የምትኖር
የልዑላን
አባት
እናመሰግንሃለን፡፡
ከእንቅልፍ
አንቅተህ
ወደዚህ
የጸሎት
ቤት
ያስገባኸን
የልዑላን
አባት
እናመሰግንሃለን፡፡”
አንተ
ወደ
እርሷ
የገሰገሰ
አይደክምም
ብለሃልና
እንለምንሃለን፡፡
እንማልድሃለን
ቃልኪዳንህን
አስብ::
ዳዊት
በመዝሙር
እንደተናገረ
ከሰማይ
ሆነህ
የመቅደስህን
አዳራሽ
ጎብኝ::
ያንጊዜ፣
አንተ
በቤተክርስቲያን
በጎበኘኸን
ጊዜ
ልጅነታችን
ይጸናል::